በመኸር ሰብል ልማት የተመዘገበው ስኬት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትልቅ ተስፋ ማሳየቱ ተገለጸ።
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/
አዲስ አበባ — በደረሱ በመኸር ሰብሎች ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ እንደሚያሳየው፣ ዘንድሮ የተመዘገበው ከፍተኛ የሰብል ምርታማነት ከተማዊ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠርና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣ አጠቃላይ ሰራተኞች፣ የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት፣ ሞዴል አርሶ አደሮችና የአካባቢው አርሶ አደሮች በተገኙበት በተካሄደው የመስክ ምልከታ ላይ እንደተገለጸው፤ ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን፣ የተሻሻሉ ዝርያዎችንና የኩታ ገጠም የአመራረት ዘዴን በሰፊው ጥቅም ላይ ማዋል መቻሉ ለምርታማነቱ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
በተለይም በዋና ዋና የሰብል ዓይነቶች ላይ የታየው ውጤታማ አፈጻጸም በምግብ ምርቶች ላይ የሚታየውን ያልተገባ የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያረጋጋው ተመልክቷል።
ወቅቱን ጠብቆ ሰብሉን ከብክነት በፀዳ መንገድ በመሰብሰብ ከተማዋ የምትፈልገውን ምርት በውስጥ አቅም መሸፈን እንደሚገባ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ተናግረዋል።
ይህ የሚታየው ውጤታማ ሰብል ከድህረ-ምርት ብክነት በፀዳ መንገድ ተሰብስቦ ከገባ የምርት ውጤታማነቱን በቀጥታ ከሸማቹ ማኅበረሰብ ጋር በማስተሳሰር የገበያ ሰንሰለቱን ለማሳለጥና የኑሮ ውድነቱን ጫና ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ሞዴል አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments