“ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!”

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

“ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!”

አዲስ አበባ፡- ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


የከተማ ግብርና ለከተማዋ ነዋሪዎች መሰረታዊ ፍጆታ እፎይታ የሰጠ ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ወጣቶች እና ሴቶች አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።


በወተት ላም እርባታ፣ በዶሮ እርባታ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በንብ ማነብ፣ በእንስሳት ማደለብ፣ … ወዘተ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል።


በተለይም የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም የከተማዋን ነዋሪዎች ከሸማችነት ወደ አምራችነት ያሸጋገረ ሲሆን፣ ከከተማ ግብርና የሚገኘው ምርት የምግብ ወጪን በመቀነስ የኑሮ ውድነትን በማቃለል አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።


ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የከተማ ግብርናውን አጠቃላይ ምርታማነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ እየተሰራ ያለው የክላስተርና የተቀናጀ ከተማ ግብርና ሥራ እና ከተማ ግብርና ለከተማዋ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ሲታይ “ግብርና ከማምረትም በላይ!” መሆኑን ያመለክታል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments