“በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ተከበረ፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የኮሚሽኑ አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
በዓሉ መከበሩ የኢትዮጵያን ህብረ-ቀለም፣ የህዝቦቿን አብሮነት፣ መቻቻል እንዲሁም የጋራ ዕድገትና ሰላም ለማጠናከር ያለመ ትልቅ ዓላማ ያለው መሆኑን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ልጋኒ ገልፀዋል፡፡
በዓሉ በስልጠናና በፓናል ውይይት የተከበረ ሲሆን የፓናል ውይይት አቅራቢዎች ብዝኃነታችንን ዕድል አድርገን፣ በሰላም ግንባታ ላይ በንቃት በመሳተፍ እና የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ዕሴቶችን በማክበር የምንመኘውን ሃገራዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል፡፡
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የልዩነት ውበታችንን ጠብቀን በምክክር ማዕቀፍ ሀገራዊ ችግሮቻችንን መፍታት እንደሚገባ አንስተዋል።
በብዝሃነት አስተዳደር፣ በጋራ መግባባት እና በይበልጥም የሰላም ባህልን በማስፈን ዙሪያ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments