የከተማ ግብርና እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክላስተር...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የከተማ ግብርና እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክላስተር ተቋማት አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


የከተማ ግብርና እና ሥራ ዕድል ፈጠራ ክላስተር በ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ90 ቀናት ንቅናቄ ዕቅድ አካል የሆነውን የ28 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የአምስቱ የክላስተሩ ተቋማት የ28 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የክላስተር አደረጃጀቱ ስራዎችን በተናበበ መልኩ ለማከናወን እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
 
በ28 ቀናት ዕቅድ አፈፃም በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን፤ በብሎክ፣ ወረዳ እና ክፍለ ከተማ ደረጃ በተደረጉ መድረኮች ከ700 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ባህል ግንዛቤ ማግኘት ችለዋል።
 
በተለይም በወቅቱ በተሰራው ሰፊ ስራ 47,232 ዜጎች ላይ አዲስ የሥራ ዕድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ 1,039 አዲስ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተዋል።
 
ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ነባር የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን ማስቀጠል፣ ለኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ የብድር መጠን ማመቻቸት፣ 205 የመሳሪያ ሊዝ ማመቻቸት፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በሴቶችና ወጣቶች ማብቃት እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፎች ተስፋ ሰጪ አፈፃፀሞች የተመዘገቡ መሆኑ በውይይቱ ተመላክቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments