"ከተማ ግብርና ዜጎችን ከሸማችነት ወደ አምራችነ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

"ከተማ ግብርና ዜጎችን ከሸማችነት ወደ አምራችነት ያሸጋግራል" — ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በም/ከንቲባ ማዕረግ የሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


በ5ኛ ዓመት 2ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የሥራ ዕድል በሌማት ትሩፋት ለሚፈጠርላቸው ከ800 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የግብዓት ድጋፍ ተደርጓል፡፡


የዕለቱ የክብር እንግዳ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፤ የከተማ ግብርና ዜጎችን ከሸማችነት ወደ አምራችነት በማሸጋገር የሥራ ዕድል የሚፈጥርና የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ ዘርፍ በመሆኑ፣ ተጠቃሚዎች ድጋፉን በአግባቡ ተጠቅመው ውጤታማ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በበኩላቸው፤ ዘርፉ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ የዜጎችን የመግዛት አቅም የሚያጎለብት መፍትሔ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዕለቱም፡-110 ዘመናዊ የዶሮ ኬጅ እና 110 ኩንታል የዶሮ መኖ ለ220 ተጠቃሚዎች፣5,500 እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎች፣ለ104 ማህበራት ዘመናዊ የንብ ቀፎ፣ እንዲሁም ለወረዳ የግብርና ኤክስቴንሽን ሥራ የሚውሉ 5 ሞተር ሳይክሎች ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments