የህገ-ወጥ እንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ግብረ-ሃይል በቁጥጥር ሥራው ውጤትማ ሥራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
የህገ-ወጥ እንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ-ሃይል እያካሄደ ባለው የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ አበረታች እና ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የግብረ-ሃይሉ ሰብሳቢ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ግብረ-ሃይሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በሚያደርገው ጥብቅ ክትትል፣ የህብረተሰቡን ጤና ለአደጋ የሚያጋልጡ በርካታ የህገ-ወጥ እርድ ሥፍራዎችን እና በህገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ሥጋ በቁጥጥር ስር በማዋል አስተማሪ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ይህ የተቀናጀ ቁጥጥር ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመግታት ባለፈ፣ በህጋዊ መንገድ በሚሰሩ ቄራዎች እና የሥጋ ነጋዴዎች ላይ የሚደርሰውን የገበያ መዛባት በማስተካከል ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የግብረ-ሃይሉ አባላት ተናግረዋል፡፡
የቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጸው ግብረ-ሃይሉ፣ ህብረተሰቡም ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ሥጋ ባለመጠቀምና ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments