ግብርና፡ ከባህላዊ እርሻ ወደ ዘመናዊ የከተማ አ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ግብርና፡ ከባህላዊ እርሻ ወደ ዘመናዊ የከተማ አብዮት!


ግብርና ትናንትና — በላብና በዕለት ድካም ብቻ የሚታወቅ፣ በገጠር መሬትና በእጅ መሳሪያዎች ተወስኖ የኖረ፣ ለከተማው ፍጆታ ብቻ የሚቀርብ ሩቅ የዕለት እንጀራ ምንጭ ብቻ ነበር።

ግብርና ዛሬ — ድንበር የለሽ፣ በቴክኖሎጂ የተዋቀረ እና በከተሞች ጭምር ሕያው እየሆነ ያለ የንግድና የፈጠራ ማዕከል ነው።

ዛሬ ግብርና ከገጠር ወጥቶ የከተማችን ጣሪያዎች፣ በረንዳዎችና ጓሮዎች ውስጥ እየተሰራ ነው። "የከተማ ግብርና" (Urban Agriculture) ከተማዎችን አረንጓዴ፣ ጤናማና የምግብ ዋስትናቸው የተረጋገጠ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል።

ዛሬ ግብርና ማለት መሬት ያለው ብቻ የሚሰራው አይደለም፤ እውቀት፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ የታከለበት የዘመኑ የኢኮኖሚ ምሰሶ ነው።

ከገጠር ማሳ እስከ ከተማ ጓሮ—ግብርና የነገን ኑሮ የምንቀርጽበት የህይወት ምንጫችን ነው!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments