የመንግስት አገልግሎት እና አሰተዳደር ሪፎርም የ...

image description
- ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የመንግስት አገልግሎት እና አሰተዳደር ሪፎርም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)



የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ዌቭ 2 ውስጥ ለገቡ ተቋማት እየሰጠ ያለውን "የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም" በማጠናከር ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት ለማረጋገጥ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ሰጥቷል፡፡

የሪፎርሙ ዓላማ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን፣ ብዝሀነትን እና አካታችነትን ያረጋገጠ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎቶች የሚያቀርብና ለልማት ስኬት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቁ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት ነው።

የሪፎርሙ ሰባት ዋና ዋና የፖሊሲ አምዶች (ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት መዘርጋት፣ የመንግሥት አደረጃጀትና አስተዳደርን ማሳለጥ፣ የሠራተኞችን ብቃት በምዘና ማረጋገጥና ማሳደግ፣ ነፃና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት፣ ብዝኃነትና አካታችነትን ማረጋገጥ፣ ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ መገንባት እንዲሁም አመራርና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር) መኖራቸውን አቶ ጌቱ ቱፋ ተናግረዋል።

የሪፎርሙ ዓላማ ብቁ የሆነ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቀልጣፋ፣ ወጭ ቆጣቢ፣ ፍትሐዊ፣ ዘመኑን የዋጀ ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት እና የተገልጋይን እርካታ ማሳደግ መሆኑን የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.