የድህረ-ምርት ብክነትን ለመቀነስ ሰብልን በወቅቱ መሰብሰብ እንደሚገባ የግብርና ባለሙያዎች አሳሰቡ፡፡
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
አዲስ አበባ ላይ 7,165 ሄክታር መሬት በመኸር ሰብል የተሸፈነ ሲሆን ለአጨዳ በደረሱባቸው አካባቢዎች አርሶ አደሮች ምርታቸውን ሳይዘገዩ በወቅቱ እንዲሰበስቡ የግብርና ባለሙያዎች አሳስበዋል።
ባለሙያዎቹ እንደገለጹት፣ ሰብሎች ከደረሱ በኋላ በማሳ ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ፣ በነፍሳት፣ በተባዮች፣ በአእዋፋት እንዲሁም በመርገፍ ከፍተኛ የድህረ-ምርት ብክነት ይከሰታል።
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእጽዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ቻላቸው ዓለም አርሶ አደሮች የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን በመከታተል እና የሰብል መሰብሰቢያ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የተደራጀ የሰው ኃይል በመጠቀም የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት መሰብሰብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
አያይዘውም ከመሰብሰብ ባለፈም ምርቱን እርጥበት በሌለውና በተዘጋጀ ንጹህ ጎተራ ወይም የማከማቻ ሥፍራ በአግባቡ ማስቀመጥ የምርት ጥራትንና ደህንነትን ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.