
በጋራ ሰርተን በጋራ ከተማችንን እናለማለን።
አዲስ አበባ፤ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ቅንጅታዊ ሥራ አፈፃፀም ግምገማ እያደረገ ይገኛል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የጋራ ዕቅዳችንን በጋራ ሰርተን ማሳካት የጋራ ተግባርና ኃላፊነታችን መሆኑን መረዳትና ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪ ከእኛ የሚፈልገውን ነገር በጋራ ሰርተን በጋራ ውጤት በማምጣት ተገልጋዮቻችንን ማርካት ይገባል ብለዋል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ በቅንጅታዊ አሰራር ዕቅድ መሰረት በ6 ወራቱ ውስጥ የነበረውን አፈፃፀም በዝርዝር አቅርበዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ለውይይት የሚሆኑ ፍሬ ሃሳቦችን አንስተው ቤቱን ለውይይት ጋብዘዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments