
የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት ቅንጅታዊ ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በቅንጅት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ እውቅና ሰጥቷል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ዕቅድ ከማቀድ ጀምሮ በእያንዳንዱ ተግባር አፈፃፀም ውጤት ላይ በወቅቱ በልኩ መነጋገር እንደምገባ ገልፀዋል፡፡
የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ በባለፉት 6 ወራት በቅንጅት በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን አንስተው አርሶ አደሩን ፍትሐዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ከመብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ ግን ቀሪ ሥራዎች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ ፋሩቅ ጀማል ከተማ ግብርናን ከማስፋፋትና ከማጠናከር አንፃር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ማስተር ፕላ ላይ ለከተማ ግብርና የተመላከቱ ቦታዎችን ለታለመላቸው ዓላማ እየዋሉ ባለመሆኑ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊያግዘን ይገባል ብለዋል፡፡
ከየተቋማቱ የመጡ የተቋማት ኃላፊዎች እና ተወካዮች ከቅንጅታዊ አሰራር ጋር በተያያዘ ያልተሻገርናቸው ችግሮች አሉ፤ ይሁንና ከኮሚሽኑ ጋር የሰራናቸው ሥራዎች ቀላል ባለመሆናቸው በቅርብ እየተገናኘን ክፍተቶችን እያረምን መሄድ ይገባል ብለዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የአርሶ አደሮች መብት ፈጠራ፣ መሰረተ ልማት፣ መስሪያ ቦታዎች ዝግጅትና አቅርቦት፣ ለማህበራት የሚደረግ ድጋፍና ክትትል፣ የፋይናንስ አቅርቦ፣ ተቋማትን የተቀናጀ የከተማ ግብርና የምርት ማዕከል ማድረግ፣ ወዘተ ልዩ ትኩረት የሚሹ በመሆናቸው ተቀራርበን በመስራት ማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments