የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በሌማት ትሩፋት ንቅናቄ በ10ሩም ወረዳ በማህበራት ለተደራጁ 50 ማህበራት የአትክልትና ፍራፍሬ ምርጥ ዘር እና የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ስርጭት አደረገ።

በፕሮግራሙ ላይ ለ50 ማህበራት 7,000 እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎች እና ምርጥ ዘር ለማህበራቱ ድጋፍ ተደርጓል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ ፋሩቅ ጀማል የከተማ ግብርና እና የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ በበኩላቸው በ10ሩም ወረዳ ለ50 ማህበራት 890 ተጠቃሚዎች 7,000 እንቁላል ጣይ የቄብ ዶሮዎችን እና የምርጥ ዘር ስርጭት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

እባክዎን እዚህ ይከተሉን!
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments