ዛሬ 26ኛውን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የአ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ዛሬ 26ኛውን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ አስጀምረናል።

የእንስሳት በሽታ በእንስሳት ተዋፅዖ ውጤቶች ምርታማነት እና በዜጎች ጤናማ አኗኗር ላይ ያለውን ቀጥተኛ ተጽዕኖ በመረዳት ችግሩን በጋራ ትብብር ልንሻገረው ይገባል፡፡

ዛሬ 26ኛውን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ አስጀምረናል።

በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ በመኖ አቅርቦትና ጥራትን ለማሻሻል በሰራነው ስራ በንጥረ ነገር የበለፀገ ምግብ በማምረት የአመጋገብ ስርዓታችንን ለማሻሻል እና የእንስሳት ጤና እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

እንደ አህጉር የሚፈትነንን የእንስሳት በሽታ ለመከላከልም ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትን ከማቋቋም አንስቶ ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነናል፡፡

የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት እንዲጠናከር በእንስሳት እና በእንስሳት ተዋጽኦ ንግድ ዘርፍ ያሉ የጤና አጠባበቅ ህግጋት መከበር ላይ እንደዚህ ያሉ ጉባኤዎች ከፍተኛ ሚና ስለሚኖራቸው ይህ ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

@ከክቡር ም/ጠ ሚኒስቴር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ

እባክዎን እዚህ ይከተሉን!
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments