መረጃ ሃብት በመሆኑ በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

መረጃ ሃብት በመሆኑ በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት መደራጀት አለበት፡፡

 

አዲስ አበባ፤ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርናከተማ  ግብርና ልማት ኮሚሽን  የአርሶ አደሮችን  መረጃ  አያያዝ  በዘመናዊ መልኩ ለማደረጀት  ሶፍትዌር  በመጠቀም  ወደ አንድ የመረጃ ቋት እያስገባ ይገኛል፡፡

 

ቀደም ብሎ በዘመናዊ የመረጃ ቋት ተይዞ ይልነበረውን አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች፣ የቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚዎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የወጣላቸው አርሶ አደሮች እና የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገላቸው ማህበራትን መረጃ ወዘተ በቴክኖሎጂ በተደገፈ በዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት የማደራጀት ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

ሥራው ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን የካ ክፍለ ከተማ 58 አርሶ አደርና 259 የአርሶ አደር ልጅ፣ የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው 13 ማህበራት እና 86 አባላት፣ ስልጠና የወሰዱ ማህበራት 86፣ የዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ  ተጠቃሚ 13፣ ኮንዶሚኒም እጣ የወጣላቸው 217፤ የቦሌ ክፍለ ከተማ 809 አርሶ አደርና 3,045 የአርሶ አደር ልጅ፣ 64 የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው ማህበራት እና 256 ማህበራት አባላት፣ ስልጠና የወሰዱ ማህበራት 256፣ የዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ 104፣ ኮንዶሚኒም እጣ የወጣላቸው 2174 ገቢ የተደረገ መሆኑን የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሳ ተናግረዋል፡፡

 

ዳይሬክተሩ የንፋስ ስልክ  ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1237 አርሶ አደርና 3,506 የአርሶ አደር ልጅ፣ የሥራ ዕድል የተመቻቸላቸው 14 ማህበራት እና 31 አባላት፣ ስልጠና የወሰዱ ማህበራት 31፣ የዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ  ተጠቃሚ 108፣ ኮንዶሚኒም እጣ የወጣላቸው 2,392፣ ኮልፌ  ክፍለ ከተማ 127 አርሶ አደርና 138 የአርሶ አደር ልጅ፣ የዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ  ተጠቃሚ 28፣ 345 ኮንዶሚኒም እጣ የወጣላቸው፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 165 የአርሶ አደር ምዝገባ፣ የአርሶ አደር ልጆች  ምዝገባ 758 አርሶ አደሮች እስካሁን ድረስ መረጃቸው  ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት ገቢ የተደረገ ሲሆን የቀሪ ክፍለ ከተሞችም የአርሶ አደር መረጃ እየተሰራ መሆኑን አቶ ረጋሣ ባይሳ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments