
የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ለብዙዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም
ሥራ ክፍላችን በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገኝቶ ሞዴል የከተማ ግብርና ሥራዎችን የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 እነ ዶ/ር እረጋሳ ጉርሙ በተቀናጀ ከተማ ግብርና ዘርፍ በአትክልትና ፍራፍሬ ቲማቲም፣ ዝኩኒ፣ ባሮ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ቃሪ፣ ኢታማሪሎ፣ ፋሽንፍሩት፣ ቻይብ (የቻይና ሽንኩርት)፣ እና በእንስሳት ዘርፍ በማድለብ፣ በወተት እና በበግ እርባታ ተሰማርተው ሰፊ ምርት ለከተማዋ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከ10 በላይ ለሚሆኑ ግለሰቦችም የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች የምግብ ፍጆታን ከመሸፈን ባሻገር ለህብረተሰቡም ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ሌላው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የኦሮሚያ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ በግቢቸው ውስጥ በጓሮ አትክልት፣ በወተት ላም እና በዶሮ እርባታ ላይ እየተሰራ ያለው ሥራ ከተማ ላይ ግብርና አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ የቀየረ ተግባር ማሳያ ነው፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አቢዮት ቅርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ የሥራ እድል የተፈጠረላቸው በ3 ማህበራ የተደራጁ 30 አባላት በጓሮ አትክልትና በእርባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ በለጠች ተሰማም በቦታው ተገኝተው ትምህርት ቤቱ ላይ እየለማ ያለውን የከተማ ግብርና ሥራ አሳይተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments