ሌብነትና ብልሹ አሰራርን እንታገላለን ተጠያቂነትን እናሰፍናለን።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 08 ቀን 2017 ዓ.ም
ለሚ እንጀራ ማዕከል በከተማችን ወይም እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ ሞዴል የሆነና ለበርካታ እናቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ ተቋም ነው።
ማዕከሉ ንፁህ የሆነ ጤፍ በመጠቀም ለዮኒቨርስቲዎች፣ ስካይ ላይትን ጨምሮ ለትልልቅ ሆቴሎች፣ ለአየር መንገድና ሌሎች የመንግስትና የግል ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ እንጀራ ያቀርባል።
ማዕከሉ ከ500 በላይ ለሆኑ እናቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ ቢሆንም አሁን ላይ በሮካታ ችግሮች ታይተውበታል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ተቋሙ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅ የውስጥ ኦዲት ባለሙያ አሰማርቶ የኦዲት ሥራ አሰርቷል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስተካከል ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በተካሄደውም የኦዲቲንግ ሥራ ማዕከሉ ከ19,579, 704, 87 ሚሊዮን በላይ ብር እዳ እንዳለበት ግኝቱ የሚያመለክት መሆኑን የኮሚሽኑ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አረጋ ፉፋ ገልፀዋል።
አቶ አረጋ ፉፋ የአደረጃጀት ክፍተት፣ የተልዕኮ አሰጣጥና የሥራ ስምሪት አለመኖር፣ የሒሳብ አያያዝ ክፍተት መኖር፣ የጨረታና የግዥ ሂደቱ አሰራርን ያልተከተለ መሆን፣ ሰነድ አልባ የግብይት ሂደቶች መታየታቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል።
አያይዘውም ደረቅ ቸክ በዘፈቀደ እየተቆረጠ ለነጋዴ እንደሚሰጥ፣ የጤፍ ግዥ ከአሰራር ውጭ እንደሚከናወን፣ የጤፍ በጣሪ ለነጋዴዎች መልሶ ገቢ እንደሚደረግና ቀጣይ ከሚገዛ ጤፍ ጋር ተቀላቅሎ እንደሚመጣ የተገኘው ግኝት አመላካች መሆኑን ተናግረዋል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እንደዚህ አይነት አሰነዋሪ ተግባር በመፈፀም በእናቶች ላብ ያልተገባ ገቢ ለማግነት መሞከር የማንታገሰው ተግባር በመሆኑ ኮሚሽኑ በየደረጃው አስተማሪ እርምጃ ይወስዴል ብለዋል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የተፈጠረው ሌብነትና ብልሹ አሰራር በእጅጉ አስነዋሪ መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህንን ማዕከል ሲያቋቁሙ የብዙ እናቶችን ሕይወት ለመቀየር እንጅ የጥቂት ጥቅመኞችን ምኞትና ፍላጎት ባለመሆኑ ኮሚሽኑ አጥፊ በተባሉ አካላት ላይ አሰተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ሰርታችሁ እንድታተርፍ ያደርጋል ብለዋል።
የማህበሩ አባላት እናቶችም ተበደልን ያሏቸውን አሰተያየቶችና ጥያቄዎች አቅርበዋል፤ የኦዲት ሪፖርቱንም በሚሉ ድምጽ አጽድቀዋል፤ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸውም ተማጽነዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤም ችግሮቻቸው ለአንድየና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲፈታ እንደሚሰሩ፤ ነገር ግን እናቶች የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ አሳስበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments