ለኤችአይቪ አጋላጭ ሁኔታዎች ላይ በትኩረት መሰራ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

ለኤችአይቪ አጋላጭ ሁኔታዎች ላይ በትኩረት መሰራት ዓለበት

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኤችአይቪ ሚኒስትሪሚንግ ፎካልፐርሰኖችና እናት አንባሳደሮች  እሮብና አርብ  ለተቋማችን ተገልጋዮች   በኤችአይቪ  ኤዲስ ዙሪያ ከ2፡30 ሰዓት በፊት ቀደም ብለው ከ15-20 ደቂቃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የኤችአይቪ ስርጭት ባለባቸው  አካባቢዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች የተሟላ የኤችአይቪ መከላከል ፓኬጅ ተግባራዊ   መደረግ እንዳለበት፤ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው አካባቢዎች ላይ ያተኮረ የኤችአይቪ ምክርና ምርመራ መስፋት እንዳለባቸው፤የኤችአይቪ ምክርና ምርመራ እና የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ህክምና አገልግሎት ትስስርን መጠናከር እንዳለባቸው፣ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍን ለማስቀረት ሁሉም ነፍሰጡር ሴቶች በቅድመ ወሊድ እንክ ብካቤ ወቅት ምርመራ እና አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማበረታታት እንዳለባቸው፤ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝባቸው ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የቲቢ እና የአባላዘር በሽታዎች ምርመረራ ማጠናከር  እና አገልግሎት ጀምረው የሚያቋርጡና የሚጠፉትን መቀነስ  ዙሪያ ውይይቱ የተካሄደ ሲሆን  ተሳታፊዎቹ  በውይይቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው  ውይይቱ መቀጠል እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments