በአገራችን ከድህረ ምርት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ች...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በአገራችን ከድህረ ምርት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች እና  የሚያስከትሏቸው ጉዳቶች  ብዙ ናቸው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

እህሉን ከማሳ በወቅቱ አለመሰብሰቡ  በአገራችን በከፍተኛ ደረጃ የሚታይ ችግር ሲሆን ይህም እህሉ በማሳ ላይ እያለ ዘሩ እንዲበተን፣ በአይጥ ወይም በወፍ እንዲባክን ወይም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ከመጣ እህሉን እስከማብቀል እና  እንዲሻግት  ሊያደርግ  እንደሚችል ይነገራል፡፡

እህሉ ተገቢው የእርጥበት ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወደ ጎተራ ማስገባት፡ የእህል ሰብሎች በአብዛኛው  ከፍተኛው የእርጥበት መጠናቸው ከ8 እስከ 12 በመቶ ሲደርስ ለማከማቸት ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ የሚመረት እህል እዚህ የእርጥበት መጠን ላይ ሳይደርስ ወቅቶ ማከማቸት በጎተራ ውስጥ ለተባይ እና ሻጋታ ክስተት ምቹ የሆነ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ እህሉ በጎተራ ውስጥ እንዳለ ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል ተብብሏል ፡፡

በተጨማሪ የከረመን እና አዲስ እህልን ቀላቅሎ ማስቀመጥ፡ የከረመ እህል ዝቅተኛ የሆነ የእርጥበት መጠን ያለው፣ በተወሰነ መልኩ የተባይ እና በሽታ ክስተት ያለበት ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል፡፡ በእንፃሩ ደግሞ አዲስ እህል ከፍ ያለ የእርጥበት መጠን ያለው እና በአንፃራዊነት ከተባይም ይሁን ከበሽታ የፀዳ ነው፡፡ 

ምንጭ ፡-ግብርና ሚንስቴር


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments