
ተቋማትን የምርት እና የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ትምህርት ቤቶች የከተማ ገብርናን እንዲተገብሩ አንዱ የምዘናው አካል በማድረጉ ትምህርት ቢሮን በራሴና በኮሚሽኑ ስም ላመሰግን እወዳለሁ፤ ዋና ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የከተማ ግብርና ሥራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የንቅናቄና የእውቅና ፕሮግራም ያዘጋጀ ሲሆን የትምህርት ቢሮ እና የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ከሚሽን አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት እና የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ተቋማት ተግባራዊ የተደረገው የከተማ ግብርና በትምህርት ሥርአቱ የተካሄደውን ሪፎርም መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ይህ ተግባር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የትምህርት ቤቶች አካባቢ ጽዱ፣ ሳቢና ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዬ ሽጉጤ ትምህርት ቤቶች ጨምሮ ከ3,000 በላይ ተቋማት የከተማ ግብርና ፕሮግራምን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የከተማ ግብርና ሥራ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚያዩበት በመሆኑ ትምህርት ቢሮ ትምህርት ቤቶችን በመመዘን ዕውቅና እንዲያገኙ በማድረጉ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በከተማ ግብርና ፕሮግራም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 35 ትምህርት ቤቶች 60 የዶሮ ኬጅ፣ በየክፍለ ከተማው 1ኛ ለወጡ ተቋማት 60 ዶሮ እና የ3 ወር መኖ እንዲሁም ከየክፍለ ከተማው 2ኛ ለወጡ ተቋማት 60 ዶሮ ስጦታ አበርክቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments