
የአቅም ግንባታ ስልጠና ክፍተትን መሰረት አድርጎ መሰጠት አለበት፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን የኮሚሽኑን ሰራተኛ የአቅም ግንባታ ክፍተት በመለየት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት መኮንን ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ባለሙያ በመጋበዝ ለዳይሬክቶሬቶች፣ ለቡድን መሪዎች እና ለጠቅላላ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ መሰረት መኮንን ስልጠናው በዙር የሚሰጥ ሲሆን አሁን በመጀመሪያው ዙር የተወሰኑ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ቡድን መሪዎች በቦሌ ዋሽንግተን ሆቴል ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሰልጣኞች ስልጠናውን በሚገባ በመከታተል በተመደቡበት የሥራ ዘርፍ ላይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሊጠቀሙበት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments