የአርሶ አደሮች መብት ፈጠራ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

የአርሶ አደሮች መብት ፈጠራ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

አርሶ አደሮች በይዞታቸው ላይ ማልማት እንዲችሉ መብት የመፍጠር ተግባራት በ8 ክፍለ ከተሞች እና በ53 ወረዳዎች ላይ በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ተግባሩ በዐብይ ኮሚቴ እና በየደረጃው ባለው የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ መዋቅር እና የኮሚሽኑ መዋቅር በጋራ ከወረዳና ከክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር በመሆን እየሰሩ መሆኑ በነበረን ምልከታ ታይቷል፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የአርሶ አደሩ መብት ፈጠራ ሥራ በየደረጃው ከስር ከስር እየተገመገመ ተፈጠሩ ለተባሉ ችግሮች ፈጣን የማስተካከያ ምላሽ እየተሰጠባቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሣ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እኩል አፈፃፀም ላይ አይገኙም፤ ለምሳሌ የካ ክፍለ ከተማ በተሻለ ሁኔታ መረጃውን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አፀድቆ ልኳል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የተወሰኑ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ላይ የአመራሩ፣ የባለሙያና የራሱ የአርሶ አደሩ ተናቦ ያለመስራት፣ አንዳንድ አመራሮች በተለይም ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ሥራውን ገምግሞና አጽድቆ መላክ ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም አቶ ረጋሣ ባይሣ ልኬት የተወሰደላቸው (ነባርና አዲስ) አርሶ አደር 14,058፣ የአርሶ አደር ልጅ 1,469 በድምሩ 15,527 መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአርሶ አደር ልማት ቡድን መሪ ወ/ሮ ደግነሽ በደዊ የመብት ፈጠራ ሥራው በኮሚሽኑ ተጀምሮ በኮሚሽኑ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ ሌሎች ተቋማት በተለይ መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣ የወረዳ እና የክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቅንጅታዊ አብሮነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ይላሉ ወ/ሮ ደግነሽ በደዊ በተለይ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ላይ ባለጉዳይን ማመላለስ፣ የተለያዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር ፍላጎትና ዝንባሌዎች መታየት፣ ኃላፊነትን አለመወጣት፣ ፋይል መደበቅና ማን አለብኝነት የታዩ ሲሆን በኮሚሽኑ ስትራቴጂክ ካውንስል ተገምግሞ የማስተካከያ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል ብለዋል፡፡

ሌላው ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ በየደረጃው ያለው አመራር፣ ባለሙያ እና ራሱ አርሶ አደሩ ይህ ሥራ ፈጥኖ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በተጠያቂነት መንፈስ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments