የግብርና ቤተሰቦቻችንን የምግብ ዋስትናን ለማረጋ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

የግብርና ቤተሰቦቻችንን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተግተን እየሰራን እንገኛለን። ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጎ ቡድን መሪነት እየተመሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተገኝተው በከተማ ግብርና የተሰሩ ሥራዎችን በመስክ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ፣ የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለሰ አንሸቦ፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ የዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደቻሳ፣  ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች በመስክ ጉብኝቱ ተሳታፊ ሆነዋል።

ልዑካን ቡድኑ እስከ ሰዓት ባለው የመስክ ምልከታው በቦሌ ክፍለ ከተማ ተገኝቶ የቦሌ ቡልቡላ ፖሊስ ጣቢያ የዶሮ እርባታና የእነ አቶ ታምራት ግስላ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ሥራዎች ጉብኝት አድርጓል።

ልዑካን ቡድኑ በመስክ ቨተመለከቱት የከተማ ግብርና ልማት እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን እና ብዙ ልምድ የሚወሸድባቸው የግብርና ስራዎችን የተመለከቱ መሆኑን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments