
ቴክኖሎጂ ከተማ ግብርናን ከማዘመን ባሻገር ምርትና ምርታማነቱን ያሳድጋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጎ ቡድን መሪነት እየተመሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተገኝተው በከተማ ግብርና የተሰሩ ሥራዎችን በመስክ የመጎብኘት ሂደቱን እንደቀጠሉ ናቸው።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ፣ የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለሰ አንሸቦ፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ የዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደቻሳ፣ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎችም በመስክ ተገኝተው የተሰሩ ሥራዎችን እያስጎበኙ ይገኛሉ።
ልዑካን ቡድኑ በመስክ በተመለከቱት የከተማ ግብርና ልማት እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን እና ብዙ ልምድ የሚወሸድባቸው የግብርና ስራዎችን የተመለከቱ መሆኑን ገልፀዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መሪ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጎ የተመለከቱት የከተማ ግብርና ሥራ ሀገራችን ለግብርናው ዘርፍ የሰጠችውን ልዮ ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀደም ብሎ ከተመለከታቸው የከተማ ግብርና ልማቶች በተጨማሪ በICT ባርክ እና በእነ ዶ/ር ረጋሣ ጉርሙ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ልማት ቦታ ተገኝተው በርካታ የግብርና ልማትን ተመልክተዋል።
የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችም ቋሚ ኮሚቴው በልማት ቦታቸው ላይ ተገኝቶ ስለጎበኛቸውና ጠቃሚ አስተያየት ስለሰጧቸው ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments