የአመራር ዑደት ያለና የሚኖር ነው፡፡

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የአመራር ዑደት ያለና የሚኖር ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም


አመራር በሰራተኞች እና በተጠቃሚዎች መካከል የጋራ የሆነ እምነት እንዲዳብርና ራዕይን እውን ለማድረግ የሚያስችል የተግባቦት ስራና ውጤታማ ተግባራትን የመምራት ችሎታ እንደሆነ ብዙ ጸሐፊዎች ይናገራሉ፡፡ 


በሌላ አገላለጽ አመራር አንድን ተቋም ከለውጡ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም የማድረግ ሂደት እንደሆነና የተቋሙ የወደፊት ስዕል ምን እንደሚመስል ግምት ውስጥ በማስገባት ሰራተኞችን ከተቋሙ ራዕይ ጋር የሚያስተሳስርና ራዕዩ እውን እንዲሆን በሰራተኞች መካከል አዎንታዊ ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው፡፡ 


አመራር ሳይንሳዊ እና ጥበባዊ የሆነ የአመራር እውቀትን፣ ክህሎትን እና አመለካከትን ተጠቅሞ አቅሙ የፈቀደለትን ሁሉ ይፈጽማል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ የአመራር ዑደት ያለና የሚኖር ነው፡፡


የአመራር ዑደቱን ተከትሎ በከተማ ግብርና ዘርፍ በም/ኮሚሽነርነት ተቋማችንን የተቀላቀሉትን አቶ መለስ አንሸቦን፣ ከተጠሪ ተቋም ወደ ማዕከል የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ሆነው የተመደቡትን ፀጋ ለማ (ዶ/ር) እና ከተቋማችን አድገው የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል ኃላፊ ሆነው የተመደቡትን አቶ አሌክስ ደመቀን መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እየተመኘን ቀደም ብሎ የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ሆነው አብረውን ለነበሩት አቶ ፋሩቅ ጀማል ደግሞ አብረውን በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከልብ እያመሰገንን በሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም ነገር እንዲገጥማቸው ከልብ እንመኛለን፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments