
የአመራሩ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ለሥራ እድል ፈጠራ እና ለሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ስኬታማነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም
የሥራና ክህሎት ቢሮ እና የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በጋራ የመጋቢት ወር የሥራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመድረኩ የ2ኛው ዙር የሌማት ትሩፋት የ45 ቀናት የንቅናቄ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከባለፈው ወር አፈፃፀም አንፃር በመጋቢት ወር በሁለቱም ዘርፎ የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡
አቶ ጥራቱ አያይዘው የሥራ ዕድል ፈጠራም ሆነ የሌማት ቱሩፋት ተግባራት ከህዝቡ ኑሮ ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ በመሆናቸው አመራሩ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው በሌማት ትሩፋት ዘርፍ ነባር የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎችን ከማስቀጠል ባሻገር በርካታ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ወደ ዘርፉ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ተጠቃሚዎች ያላቸውን አቅምና ልምድ በመጠቀም የተቀናጀ የከተማ ግብርናን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በአመራሩ በኩል በቅርብ ሆኖ መደገፍ እና መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments