በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  አበረታች የአር...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  አበረታች የአርሶ-አደርና የከተማ ግብርና ልማት ሥራዎች  እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ


-------------------------
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ባደረገው የመስክ ምልከታ አበረታች የከተማ ግብርና ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጿል። 

ቋሚ ኮሚቴው የኮሚሽኑን የስምንት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ያዳመጠ ሲሆን፤ ተግባራዊነቱንም ለማረጋገጥ በከተማዋ እየተሰራ ያለውን  የከተማ ግብርና ስራ ተመልክቷል። 

የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ቡድን አስተባባሪ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጉ  የእንስሳትና የዶሮ ዕርባታ ልማት ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በአትክልት ልማት እና በከብት ማድለብ ስራዎችም አበረታች ስራዎች መከናዎናቸውን የቡድኑ አሰተባባሪ ገልጸዋል ። 

በኮሚሽኑ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በማስፋፋት ህብረተሰቡ የግብርና ምርቶችን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ ከማድረግ ረገድ ኮሚሽኑ በትኩረት መስራት እንዳለበት የተከበሩ አቶ ተስፋዬ  ጠቁመዋል። 

የኮሚሽኑ የአርሶ አደር መልሶ ማቋቋም ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ  ኮሚሽኑ በልማት ተነሽ የሆኑ 43 ሺህ  አርሦ አደሮችን በማደራጀት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል ።
እንዲሁም ኮሚሽኑ በከተማዋ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments