የሌማት ቱሩፋት መርሐ ግብር ዜጎች  በምግብ ራሳ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የሌማት ቱሩፋት መርሐ ግብር ዜጎች  በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤መጋቢት ቀን 24/2017 ዓ.ም

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 5ዙር የሌማት ቱሩፋት ፋሚሊ ቢዝነስ የ5000 ዶሮዎች፣ 100 ኬጆችና የዶሮ መኖ  ለወረዳው ነዋሪ ሴቶችና ወጣቶች አሰራጨ።

በስርጭቱ መርሐ ግብር የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ መንግስት ከዚህ ቀድሞ ከሰብል ግብርና ውጪ ይታሰብ ያልነበረውን አመለካከት በመቀየር ከገጠር አልፎ በከተማ የሌማት ቱሩፋት መርሐግብርን በመዘርጋት ዜጎች በምግብ ራሳቸውን ከመቻል አልፈው የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ማድረጉን ተናግረዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ውጤት እያመጣ ይገኛል ከነዚህ ውስጥ በከተማ ግብርና የሌማት ቱሩፋት መርሐ ግብር አንዱ ነው። በተለይም ሴቶችና ወጣቶች በዘርፉ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ ሲሆን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የዛሬው ፕሮግራምም የዚሁ ተግባር ግንባር ቀደም ማሳያ ነው ብለዋል።

የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጫላ ቸሩም ቂርቆስ የአዲስ አበባ ፈርጥ መሆኗን አንስተው የቂርቆስ ፈርጥ የሆነው ወረዳ 03 አስተዳደርም የከተማችንን የዕድገት ጉዞ ለማፋጠን የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።


የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር በዛሬው ዕለት በ2017 በጀት ዓመት ለ5ኛ ጊዜ በፋሚሊ ቢዝነስ ለተደራጁ 500 ወጣትና ሴት ነዋሪዎች 5000 ዶሮዎችን ከነኬጂያቸው አሰራጨቷል።

በስርጭት መርሐግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ፣ የቂ/ክ/ከ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ፣ የቂ/ክ/ከ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ፣ የቂ/ክ/ከ ም/ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍትህአለው ከፊያለው፣ የቂ/ክ/ከ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በለጠች ተሰማ፣ የወረዳ 03 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጫላ ቸሩ፣ የወረዳ 03 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት ተስፋዬን ጨምሮ የወረዳው አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ምንጭ፡-ቂርቆስ ወረዳ 03 ኮሙኒኬሽን


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments