
የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ከምናለማው የመኸር እርሻ የተሻለ ምርት ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ፤መጋቢት ቀን 24/2017 ዓ.ም
ለመኸር እርሻ አገልግሎት የሚውል የምርጥ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት መቅረብ አለበት፡፡ ለመኸር እርሻ አገልግሎት የሚውል የምርጥ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ዝግጅት በመኸር ሰብል አብቃይ አካባቢዎች በስፋት ይተገበራሉ፡፡
ከአቅም ግንባታ አኳያ ወቅቱ የሚጠይቀውንና የአገሪቱ ልማት የደረሰበትን ደረጃ መሰረት በማድረግ ለግብርና ባለሙያዎችና ለአርሶ አደሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቢሰጥ የተሸለ ምርት ያስገኛል፡፡ስልጠናዎችን በዋናነት በጅምላ ከመስጠት ይልቅ አካባቢያዊ ስነ-ምህዳርን መሰረት በማድረግ በየአካባቢው የሚለሙ ዋናዋና ሰብሎችን በመለየት በየዘርፉ እንዲሰጡ ማድረጉ የተሻለ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አርሶአደሩ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን መዝራት እንዲችልና አዋጭነቱም የተሻለ መሆኑ በመታመኑ እነዚህን ሰብሎች እንዲለዩ ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments