
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን አምራቾች እንቅስቃሴ ተጎበኘ
አዲስ አበባ ፤መጋቢት26 ቀን 2017 ዓ.ም
በቂርቆስ ወረዳ 02 የሚገኘው በሰዓት ከ20 እስከ 100 ኩንታል ድረስ የሚያመርት የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን ማምረቻ ፋብሪካ እና ኤሌክትሮ ሜክ ኢንጂነሪንግና አግሮ ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ በሚል ስያሜ የሚጠራው ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል፡፡በመሆኑም 28 አይነት ምርቶችን የሚያመርት ሲሆን ለ40 ዜጎችም የስራ እድል የፈጠረ ነው። ትኩረት ለተሰጠው የከተማ ግብርና ስራ በተለይም በእንሰሳትና በዶሮ እርባታ ዘርፍ ለተሰማሩ ነዋሪዎች ትልቅ መፍትሔን የሚያመጣ ነው ተብሏል።በተጨማሪም ከመኖ ማቀነባበሪያ ማሽኑ በተጨማሪ የቆጮ ምርትን በዘመናዊ መልኩ ማዘጋጀት የሚችል ማሽን ማምረት መጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments