
ሥራን ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበል ባህል መሆን አለበት።
-------------------------
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የዘጠኝ ወር ሥራ አፈፃፀማችንን ስንገመግም ምን አቅደን ምን ቀርቶናል ብሎ ከማየት ባሻገር በቀሪ 90 ቀናት ውስጥ ዕቅዳችንን እንዴት ማሳካት እንዳለብን ስትራቴጂ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል።
ሪፖርት በየደረጃው ጥራቱንና ወቅታዊነቱን ጠብቆ ከላይ እስከታች ተናባቢ ሆኖ መቅረብ እንደሚገባው ተናግረዋል።
አክለውም ሥራ ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበልን ባህል ማድረግ እና ዕቅድን የሥራ መመሪያ አድርጎ መውሰድ ከሁሉም በየደረጃው ካለ አመራር እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው 663,805 ነባር የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን በእንስሳትና እጽዋት ሃብት ልማት ማስቀጠል የተቻለ ሲሆን በርካታ አዲስ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎችን ወደ ዘርፉ ማስገባት ተችሏል።
ሌላው በ9 ወራት ሥራ አፈፃፀም ላይ እንደተመላከተው ለበርካታ ዜጎች በዘርፉ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ በዚህ ልክ ሥራችንን መገምገማችን ተገቢ ነው፤ ነገር ግን የጠራ መረጃ ይዞ ከላይ እስከታች የተናበበ ሪፖርት አዘጋጅቶ መቅረብ በየደረጃው ያለን አመራሮች መሆኑን መረዳት ይገባል ብለዋል።
ሌላው በየደረጃው ያለው አመራር (ከስትራቴጂክ አመራር እስከ ቡድን መሪ ያለው) ከጠበቂነት ወጥቶ፣ አቀናጅቶ እየመራ የሚሄድ፣ ተልዕኮ የሚቀበል፣ የመፍትሔ አማራጮችን የሚያመጣ መሆን ይገባዋል ብለዋል።
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሸቦ ግብርና በባለሙያ መመራት ያለበት ጉዳይ በመሆኑ የድጋፍና ክትትል አግባባችን ተጨባጭ ውጤት ማምጣት የሚችል መሆን ይገባዋል ብለዋል።
የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታሁን አበበ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ታግሎ ከማስቀረት አንፃር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው አንዳንድ ሥራ ክፍሎች ላይ ግን በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰዱ መሄድ እንደሚገባ አንስተዋል።
የሰርተፊኬሽን፣ ኢኒስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ሥራዎችን በመናበብና በመተጋገዝ ከሰራን ዕቅዳችንን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ማሳካት እንችላለን ብለዋል።
ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎችም በዚህ ልክ ሥራ መገምገሙ መልካም መሆኑን አንስተው መስተካከል የሚገባቸው ሥራዎች ግን ልዮ ትኩረት ተሰጥቷቸው በጊዜ መታረም አለባቸው ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ዕቅድን የሥራ መመሪያ በማድረግ ሥራዎችን ከማዕከል እስከታችኛው መዋቅር ካስኪድ በማድረግ ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበል የዚህ አመራር፣ ዳይሬክተርና ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት መሆኑን መረዳት ይገባል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments