ኮሚሽኑ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ኮሚሽኑ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም


የከተማ ግብርና ልማትን ለማስፋፋት፣ የነዋሪዎችን ተሣታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማጠናከር  በኤም.ኤስ.ኤ ንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እና በኮሚሽናችን መካከል የእንስሳት መኖ ግብይት የሥራ ስምምነት ተደርጓል፡፡ 


ስምምነቱ ለቀጣይ ሦስት ወራት የሚቆይ በእንስሳት መኖ ዋጋ ማሻሻያ መሰረት ለእንስሳት አርቢዎች ለማቅረብ እንዲቻል ዋጋን በተመለከተ ኮሚሽናችን ባደረገው ወቅታዊ የገበያ ጥናት መሰረት የፋብሪካ ዝቅተኛ ዋጋን መነሻ ያደረገ እንዲሆን ተወስኗል፡፡


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ከመኖ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ አርቢዎች ሰፊ ጥያቄ ያላቸው መሆኑን አንስተው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም ከኤም.ኤስ.ኤ ንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር በተደረገ ድርድር ኮሚሽኑ በዳሰሳ ጥናት ካገኘው ከፋብሪካ ዝቅተኛ ዋጋ በኮተቤ መጋዘን 100 ብር እንዲውም በእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል 300 ብር በመቀነስ የግብይት የሥራ ስምምነት የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ሌላው ያነጋገርናቸው የእንስሳት ግብዓትና ቴክኖሎጂ አቅርቦት አመቻች ቡድን መሪ አቶ ሃይሉ ቀዲዳ በእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል 300 ብር ከፋብሪካ ዝቅተኛ ዋጋ በመቀነስ ለማህበራቱ እንዲቀርብ ስምምነት የተደረሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


አክለውም በኮተቤ መጋዘን ላይ 100 ብር ከፋብሪካ ዝቅተኛ ዋጋ በመቀነስ እንዲቀርብ የጋራ ስምምነት የተደረገ በመሆኑ ተጠቃሚዎች በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት መስተናገድ አለባቸው ብለዋል፡፡
በዚህ መሰረት የመኖ አቅርቦቱን እና ግብይቱን ኮሚሽኑ በሚዘረጋው ትስስር መሠረት ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንም አቶ ሃይሉ ቀዲዳ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments