
በባለፈው 9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም 567 ቅሬታዎች ምላሽ ያገኙ መሆኑ ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በባለፉት 9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም 584 ቅሬታዎች ቀርበው 567ቱ ምላሽ ያገኙ ሲሆን 17ቱ በሂደት ላይ መሆናቸውን የቅሬታና አቤቱታ አቀባበልና አፈታት ሕግ ምግክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በዳዳ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የቀረቡት ቅሬታዎች የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩና አሁን በአመራሩ ግልጽ ውሳኔ ሰጭነት ምላሽ ያገኙ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የቅሬታ አቀባበልና አፈታት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ጌታሁን የቀረቡት ቅሬታዎች ይዞታየ ይረጋገጥልኝ፣ መሬቴ መሬት ባንክ ገባብኝ፣ ካሳና ምትክ ቦታ አልተሰጠኝም፣ የልማት ተነሺ አርሶ አደር ስሆን አልተመዘገብኩም፣ የጋራ መኖሪያ ቤት የውርስ ጉዳይ፣ ያለአግባብ መብቴ ተወሰደብኝ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት ሊሰጠኝ ይገባል የሚሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ አበባ ጌታሁን የቀረቡት ቅሬታና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ፣ በቃል፣ በጽሑፍ፣ ለፍርድ ቤት የሕግ ምክር አገልግሎት በመስጠት፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ እና ቅንጅታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡
አቶ ታደሰ በዳዳ ስትራቴጂክ አመራሩ ለቀረቡ ቅሬታዎች እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአካል ተጠቃሚዎች የሚገኙበት አካባቢ ድረስ በመሄድ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ አበባ ጌታሁን ዳይሬክቶሬቱ ከስትራቴጅክ አመራሩ ጋር በመሆን ምላሽ ከሰጠባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ለበርካታ ጉዳዮች ለፍርድ ቤት ማብራሪያና ምላሽ የተሰጠበት ሁኔታም መኖሩን ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments