value="
የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
ከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ የአይቻልምን መንፈስ በመስበር 2010 ዓ.ም ከነበረው ከ150 ሺህ ያልበለጠ የከተማ ግብርና ተጠቃሚ ዛሬ ላይ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ተችሏል፡፡
የከተማ ግብርና ሥራዎችን የበለጠ ለማዘመን፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብርን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ልጋኒ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ሐሙስ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም የሥራ ዕድል ለተፈጠረላቸው ተጠቃሚዎች 110 ዘመናዊ የዶሮ ኬጅ፣ 110 ኩንታል የዶሮ መኖ፣ 5,500 እንቅላል ጣይ ዶሮ፣ 180 ዘመናዊ የንብ ቀፎ እና ለወረዳዎች ለግብርና ኤክስቴንሽን ሥራ የሚውል 5 የሞተር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙም ላይ የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ተጠቃሚዎች በተገኙበት ከተማ አቀፍ የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡
አቶ መሐመድ በሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
"
Related Events
- የፌዴራል የሚኒስቴሮች ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ጉብኝት ያደርጋሉ